Script 1
[ይህ ቅጂ በእኛ ምርት ቪዲዮ ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል። የተነቃቃ፣ ደስ የሚል እና የቋንቋ ብቃት ያለው እንዲመስል እንፈልጋለን]
የባለሞያ የድምጽ ስራ ለማሰራት እኛ ምርጥ የሆንነው ለምንድን ነው?
ሲጀመር፣ በጥራት ቁጥጥር ቡድናችን እይታ ውስጥ ያለፉ ጥራት ያላቸው የድምጽ ስራዎችን ብቻ እናስረክባለን። በተጨማሪም፣ የድምጽ ስራ ከያኒዎቻችን ለእርስዎ በብዙ ቋንቋ አማራⶐች ያሏቸው ሲሆን፣ የተለያዩ የድምጽ አይነቶች እና ተመጣጣኝ የሆኑ ዋጋዎች አሏቸው! በዚያ ላይ፣ ፕሮጀክቶቻችንን በእርካታ ማረጋገጫ ዋስትና የሚሰጣቸው ሲሆን፣ በውጤቱ ደስተኛ ካልሆኑ፣ የዝግጅት አስተዳደር ቡድናችን ገንዘብዎ ተመላሽ እንዲሆንልዎ የሚያደርግ ይሆናል። [ከእያንዳንዱ ቃል በኋላ አፍታ ጊዜ ይቆዩ] ምንም ጥያቄ አይጠየቁም
የ ደንበኞች ድጋፍ እጅግ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው፤ ቡድናችን በደስታ እርስዎን ይረዳዎታል። [በእኛ ዘንድ ያለዎ ተሞክሮ፣ ጣጣ ያሌለው እንደሆነ፣ ብቃት ባላቸው ባለሞያዎች አገልግሎት እንደሚያገኙ [እዚህ ጋር ለአፍታ ጊዜ ይውሰዱ] እና ተዝናንተው አገልግሎት እንደሚያገኙ እናረጋግጣለን!
Script 2
[ይህ ቅጂ በእኛ ማርኬቲንግ ዘመቻ ቪዲዮ ላይ ጥቅም ላይ ይውላል። ታሪክዊ፣ ትኩረት የሚስብ እና በጥቂቱ ደግሞ ሚስጥራዊ እንዲመስል እንፈልጋለን።]
የድምጽ ስራዎችን ለማግኘት ከባድ በሆነበት አለም። የድምጽ ስራን መስራት አዳጋች እና ውድ በሆነበት አለም፣ አብዮት ለማስነሳት ወስነናል!
ጉዞው ቀላል አልነበረም፣ ነገር ግን ከመቼውም ይልቅ ብርቱዎች ነን።
ደረጃ በደረጃ፣ የድምጽ ስራ ኢንዱስትሪውን ወደቤትዎ ለማምጣት ዲጂታል የሆነ አገልግሎት ፈጥረናል። በዚህ ተልእኮ ውስጥ እርስዎን ያካተተን ሲሆን፣ በዚህ ህልም ውስጥ የድርሻዎን እንደሚወጡ እንተማመናለን።
ወደ ኋላ የለም።
መጣን፣ አለምን ቀየርን፣ ላንጠፋ[ለአፍታ ጊዜ ይወሰዱ] እዚህ አለን።
የድምጽ ስራ ኢንዱስትሪውን ወደ እጅዎ መዳፍ እያመጣነው ነው።